FSD Ethiopia Launches BimaLab Insurtech Accelerator to Foster Innovation in Ethiopia’s Insurance Sector

FSD Ethiopia, ESX Collaborate to Develop Rulebook for Capital Market

Addis Ababa, Ethiopia, December 6, 2023 – The BimaLab Ethiopia Insurtech Accelerator, an initiative run by Financial Sector Deepening (FSD) Ethiopia, is poised to launch on December 6th, 2023, marking a major step towards fostering innovation in Ethiopia’s nascent insurance market.

 

The program, initially initiated by FSD Africa and later adopted by FSD Ethiopia with support from the Bill and Melinda Gates Foundation, aims to empower insurtechs and address the unique challenges faced by the Ethiopian insurance industry.

 

Recognizing the need for innovative insurance solutions, particularly for low-income households, BimaLab Ethiopia aims to empower startups in overcoming obstacles such as limited resources, technical expertise, and regulatory support.

 

Within the framework of the program, a rigorous selection process has led to the careful curation of 15 startups and corporations from different parts of Ethiopia, all poised to drive profound changes in the insurance landscape. Among the chosen participants, four are insurance companies, while the remaining 11 represent startups.

 

“BimaLab Ethiopia is a testament to our commitment to inclusive financial solutions. This program will empower Ethiopian startups to drive change in the insurance landscape. With current progress in digital financial services in Ethiopia, it is time the Insurance sector takes advantage of innovation to expand its reach,” states Abel Taddele, Director, Financial Inclusion, FSD Ethiopia.

 

“Insurtech initiatives are important for expanding insurance access to underserved communities in Ethiopia. By fostering innovation, BimaLab can help develop new products and solutions to reach more Ethiopians,” says Belay Tulu, Director, Insurance Supervision Directorate at the National Bank of Ethiopia.

 

With an understanding that the Ethiopian market is still evolving, BimaLab Ethiopia welcomes startups at various stages of maturity, guiding them through a journey of discovery, validation, and innovation.

 

“BimaLab brings a wealth of experience in driving insurtech innovation. We are excited to witness the impact this program will have on the Ethiopian ecosystem,” adds Elias Omondi, Principal, Innovation for Resilience, from FSD Africa.

The heart of BimaLab Ethiopia lies in its selection process, which identifies businesses with coherent problem-solving ideas. The criteria encompass a commitment to addressing real issues in the insurance industry, innovative use of technology, and a clear demonstration of financial inclusion and social impact.

 

“Innovation is the key to addressing the needs of low-income households. BimaLab Ethiopia’s mission to support the development of innovative pro-poor products aligns with our vision to drive financial inclusion in Ethiopia,” says Edom Tesgaye, Senior Program Officer at the Bill and Melinda Gates Foundation.

 

BimaLab Ethiopia takes an educational and simplified approach to make insurtech innovation accessible. Startups not only have the opportunity to grow their ideas into sustainable businesses but also receive support in navigating the regulatory landscape and forming impactful partnerships.

 

BimaLab supported 63 insurtechs, leading to the formation of 20 strategic partnerships and development of 43 insurance products, reaching over 3,000,000 customers, while raising over USD 10 million to enhance insurance accessibility across 10 African countries.

 

“BimaLab is not just an accelerator; it’s an educational journey. We’re here to guide and equip startups for success,'” says Tonia Mutiso-Kariuki, Program Lead from Tellistic Technologies.

 

Beyond business growth, BimaLab Ethiopia aims to foster resilience and inclusivity, with a special emphasis on solutions that strengthen the resilience of women and youth and promote diversity in leadership.

 

Ethiopia’s insurance penetration is below one percent and the industry is behind in terms of innovation and digital solutions, emphasizing the need for disruptive solutions to increase insurance outreach.

 

For media inquiries or interviews, please contact Samson Berhane, at +251937 447 258

READ IN AMHARIC / በአማርኛ ያንብቡ

ኀዳር 26፣ 2016 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጲያ

 

በፋይናንሺያል ሴክተር ዲፕኒንግ (ኤፍ.ኤስ.ዲ.) ኢትዮጵያ የሚመራው የቢማላብ ኢንሹርቴክ አክስላሬተር ፕሮግራም በህዳር 26፣ 2016 የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ተቆጣጣሪ ባለስልጣኖች በተገኙበት በይፋ ተጀመረ።

በመጀመሪያ በኤፍኤስዲ አፍሪካ በአህጉር ደረጃ ተተግብሮ በኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ ወደ ስራ የገባው በቢል ኤንድ ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን አጋሮች የተደገፈው ፕሮግራሙ፤ ዓላማው በኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ዘርፍ ላይ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ አካታች መፍትሄዎችና ፈጠራዎችን በማጎልበት የአገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ነው።

በፈጠራ የታገዙ የኢንሹራንስ መፍትሄዎች በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ያላቸውን አስፈላጊነት በመገንዘብ ወደ ትግበራ የገባው ቢማላብ ኢትዮጵያ፤ የፈጠራ ባለቤቶች የሆኑ መፍትሄ ፈጣሪዎች (ስታርትአፖች) የሚገጥሟቸውን እንደ ፋይናንስ እና የሰለጠኑ ባለሙያዎች እጥረት ያሉ መሰል ችግሮችን የሚፈቱበትን መንገድ ለማሳየት ያለመ ፕሮግራም ነው።

ፕሮግራሙ ላይ የሚሳተፉ 15 መፍትሄ ፈጣሪዎች የተመረጡ ሲሆን የተለያዩ ስልጠናዎች በመውሰድ በመጨረሻም አሸናፊዎች የገንዘብ ተሸላሚ የሚሆኑ ይሆናል። ከተሳታፊዎቹ ውስጥ 11 የሚሆኑት ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች (ስታርታፕ) ሲሆኑ አራት የሚሆኑት ደግሞ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ናቸው።

በኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አቤል ታደለ “ቢማላብ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የፋይናንሺያል መፍትሄዎችን ለማምጣት ያለንን ቁርጠኝነት ማሳያ ነው” ብለዋል።

ይህ ፕሮግራም በጅምር ያሉ የፈጠራ ሀሳቦች ከታገዙ በኢንሹራንስ ዘርፍ ላይ ስር ነቀል ለውጥ ማማጣት እንዲችሉ ያለመ ነው ያሉት አቶ አቤል የኢንሹራንስ ዘርፍ ተዋንያኖች አሁን በኢትዮጵያ ያለውን የዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ ዕድገት እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድና ፈጠራን በማከል ተደራሽነታቸውን ማስፋት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የኢንሹራንስ ዘርፍ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በላይ ቱሉ “በፈጠራና በቴክኖሎጂ የታገዙ ሀሳቦች በኢትዮጵያ ውስጥ የኢንሹራንስ አገልግሎት በሌለባቸው ቦታዎች ላይ ተደራሽነትን ለማስፋት ጠቃሚ ናቸው” ብለዋል።

“በዚህ ረገድ ቢማላብ ኢትዮጵያ ፈጠራን በማጎልበትና አዳዲስ አገልግሎቶች እንዲዳብሩ በማድረግ ብዙ ኢትዮጵያውያንን ለመድረስ ከፍተኛ ዕገዛ ያደርጋል” በማለት አክለዋል።

የኤፍኤስዲ አፍሪካ ኢኖቬሽንና ሪዚሊየንስ ፕሪንስፓል ኤሊያስ ኦሞንዲ እንደተናገሩት “ቢማላብ የኢንሹራንስ ፈጠራን ከማሳደግ አኳያ ከዚህ ቀደም በነበሩ ተመሳሳይ ፕሮግራሞች ላይ አሳይቷል። በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ዘርፍ ላይ የሚገጥሙ ተግዳሮቶች የሚፈቱበትን መንገዶች በመጠቆም የመፍትሄ አካል ይሆናል” በማለት አክለዋል።

በ10 አፍሪካ አገራት ተሞክሮ በኢንሹራንስ ዘርፍ ላይ ውጤታማነቱ የተረጋገጠው ቢማላብ 63 የኢንሹራንስ ቴክኖሎጂዎችን በመደገፍ ለውጤት ያበቃ ፕሮግራም ሲሆን 43 አዳዲስ ኢንሹራንስ አገልግሎቶች ወደ ስራ እንዲገቡ አድርጓል። ከተጠቃሚዎች ረገድ ከሶስት ሚሊየን በላይ ደንበኞች ጋር ተደራሽ በመሆን ከ10 ሚሊየን ዶላር በላይ ፈንድ ማሰባሰብ እንዲቻል አስችሏል።

“አዳዲሰ ፈጠራዎች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ፍላጎት ለማሟላት አይነተኛ ሚና ይጫወታሉ“ ያሉት የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ከፍተኛ ፕሮግራም ኦፊሰር ኤዶም ጸጋዬ “የቢማላብ ኢትዮጵያ ዋና ተልዕኮ የሆነው የዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ከፍሎች ላይ ያተኮሩ መፍትሄዎቸን ማገዝ አና ማብቃት ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የፋይናንስን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ  ካለው ራዕይ ጋር አብሮ የሚሄድ ነው” ብለዋል።

“ቢማላብ ኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ፈጠራን በመደገፍ የመድን ሽፋን አገልግሎትን ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ አስተማሪ ነው“ በማለት ያከሉት ደግሞ የቴሊስቲክ ፕሮግራም መሪ የሆኑት ቶኒያ ሞቲሶ ካሪኡኪ ናቸው።

በኤፍ.ኤስ.ዲ ኢትዮጵያ የሚመራው ቢማላብ ኢትዮጵያ ሴቶችን እና ወጣቶችን የመፍትሄ አካል በማድረግ የኢንሹራንስ ተደራሽነትን ለማስፋት ያለመ ፕሮግራም ነው።

ለሚዲያ ጥያቄዎች ወይም ቃለመጠይቆች እባክዎን ሳምሶን ብርሃኔን በ +251937 447 258 ያግኙ።

About us

FSD Ethiopia is an agency that aims to support the development of accessible, inclusive, and sustainable financial markets for economic growth and development. O

prime@qodeinteractive.com

+381 123 456 677

Mon - Sat 8.00 - 18.00

Sunday closed